ቅዳሜ፣ ህዳር 16 2019

Kirchgemeindehaus Johannes, Wylerstrasse 5, 3014 Bern

የጋራ ከተማ ሰዎች በነጻነት ያለምንም ፍርሃት የሚንቀሳቀሱበት እና ማንም ወረቀት ወይም የአኗኗር ሁኔታ የማይጠይቅበት ነዉ:: ከዚህ ቀደም በባስል፣ በዙሪክ፣ በበርሊን፣ እና ሊፕዚግ ዉስጥ የከተማ የጋራ ካርታዎች አሉ በዚህም በጋራ ትብብር ላይ የተመሰረተ መዋቅር፣ በፖለቲካ እንዲሁም በፍላጎት ተነሳሽነት ከክፍያ ነጻ ቅናሾች እና የከተማ የህዝብ ቦታዎች ተገልጧል::

እኛም ለበርን ከተማ ተመሳሳይ ነገር ማዘጋጀት እንፈልጋለን:: ዓላማዉም የተለያዩ የበርን የጋራ ቦታዎች እንዲታዩ፣ አዳዲስ ተደራሽነቶችን ለመክፈት፣ ከሁሉም በላይ እርስ በርስ ለመተዋወቅና ትስስርን ለመፍጠር ነዉ:: እኛ የጋራ ከተማ ካርታን የምናየዉ እንደአንድ ጠንካራ ጽንሰ ሀሳብ ከማዳበር ራዕይ ጋር እና የከተማችንን የጋራ መሰረተ ልማት የማሳደግ ሂደት አድርገን ነዉ›› ምክንያቱም በበርን የሚኖሩ ሰዎች ምቾት ሊሰማቸዉና ሊሳተፉ እንዲሁም ከየት መጡ የሚለዉ እና ምን ያህል ገንዘብስ አላቸዉ የሚለዉ ችግር ሳይሆንባቸዉ የጋራ ከተማዉን ቅርጽ ሊቀርጹ ይገባል:: 

ስለዚህም ይህንኑ ሀሳብ ለመወያየት እና የመጀመርያዉን እቅድ ለማዉጣት ሁላችሁንም ቅዳሜ ህዳር 16 ከሰዓት በኋላ ባለዉ የዉይይት ጊዜ እንድትሳተፉ ጋብዘናል::

በጋራ የከተማ ካርታዉ ሂደት ዉስጥ Wir alle Sind Bern, Solidaritätsnetz Bern እና Migrant Solidarity Network ተሳትፈዋል

1:30 – 2:15 pm ሀሳቡን ማስተዋወቅ፣ እርስ በእርስ መተዋወቅ እና ከሌሎች ከተሞች የሚገኙ  አክቲቪስቶች የሚሰጡ አስተዋጽኦዎች

2:15 – 3:00 pm የሀሳብ ልዉዉጥ

3:00 – 3:30 pm እረፍት ከ ሙዚቃ ጋር እንዲሁም የፐርሺያ ሻይ እና ኩኪሶች

 3:30 – 4:30 pm ሀሳቦችን መሰብሰብ እና የመጪ እቅዶችን ማቀድ